➡ “ሀገር ውስጥ እያሉ ‘በሌሉበት ክስ ሊመሠረትባቸው መሆኑ’ አነጋጋሪ ሆኗል” ሲል አዲስ አድማስ በዛሬ ዕትሙ አስነብቧል።
የቀድሞው የብሔራዊ መረጃ እና ደህነንት መሥሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተር የነበሩትና ለዜጎች የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ሞት ተጠያቂ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ፤ በሚቀጥለው ሳምንት በሌሉበት ክስ ሊመሰረትባቸው መሆኑን ያልተገለጹ ምንጮቹን ጠቅሶ አዲስ አድማስ አስነብቧል።
በደህንነት መስሪያ ቤት የሀላፊነት ቆይታቸው ‘ከመንግስት እውቅና ውጪ የራሳቸውን እስር ቤት በመፍጠርና ከህግ ትዕዛዝ ተቃራኒ በሆነ መልኩ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት የሚጣረሱ ድርጊቶች እንዲፈጸሙ ትእዛዝ ሰጥተዋል፤ በቀጥታም ተሳትፈዋል’ ተብለው የተጠረጠሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ የትግራይ ክልል መንግስት ከለላ ስለሰጣቸው ሊከሰሱ
አለመቻሉን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ለፓርላማ መናገራቸው ይታወሳል፡