፨፥፨፥፨፥፨፥፨፥፨፥፨፥፨፥፨
በአንዳርጌ ፍጡሩ (ዶ/ር)
ሰሞኑን ኤርሚያስ ለገሠ.. ዶክተር ዐቢይ ላይ ድብቅ የ3 ሠዓት ቪዲዮ አለኝ ማለቱን ተከትሎ ብዙዎች ለዶ/ር ዐቢይ የወገብ ቅማል ሆነባቸው እያሉ ሲጠይቁ …ገሚሱ ሲወቅሱ፣ ገሚሱ ሲወቅሱ አየሁና እኔም የማውቀውን እውነት ላካፍላችሁ ወደድሁ፡፡በነገራችሁ ላይ ዶክተር ዐቢይ በቪዲዮ ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው (ብላክ ሜል) ሲደረጉ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ በመሆ ጉዳዩን በጥልቀት ለመርመሬ ምክንያት ሆኖኛል፡፡ ከዛሬ ዓመት በፊት የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ለመወዳደር ዶ/ር ዐቢይ በእጩነት በቀረቡ ጊዜ የቀድሞው የደህንነቱ ሹም ጌታቸው አሰፋም ዶክተር ዐቢይ ላይ በድብቅ የተቀረጸ የድምጽና የምስል ማስረጃ አለኝ በማለት ዶክተሩን በማስፈራራት ቀዳሚው ሰው ሲሆን አሁን ደግሞ ዓመቱን ጠብቆ ኤርሚያስ ይሄን የቪዲዮ ጌም ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ ሚስጥር በተወሰነ መልኩም ስለማውቅ ውቅ እና የሀገሪቱን ፖለቲካ በንቃት ስለምከታተል የኤርምያስን ማስፈራሪያ እንደ ባዶ ጪከት ቆጥሬ ባልሰማ ባላየ ማለፍ አልተቻለኝም፡፡ በተለይ ዐቢይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ተገፋሁ ብለው ያኮረፉት አቶ በረከት በተደጋጋሚ ወደ መቀሌ በመብረር ጌታቸው አሰፋ ጋር ጠንካራ ግንኙነት መስርተው እንደነበር እና ብዙ ውጥኖች ወጥነው እንደነበር ይነገራል፡፡ የበረከት ሳይጠበቅ መታሰር ጌታቸውን ለበቀል እንደሚያነሳሳው ሳይታለም የተፋታ ነው፡፡ ኤርሚስ ከበረከት ሰምዖን ጋር ያለውን ታማኝነት ዘመን የማይሽረው ወዳጅነት ከላይ ከጠቃቀስኳቸው ነግሮች ላይ በመደመር “የጌታቸው አሰፋ እና የኤርሚያስ ለገሠ ቪዲዮዎች የሚያገናኛቸው ቀጭን መንገድ ይኖር ይሆን.. “ ብየ በመጠየቅ መረጃዎችን ማሰባሰብ ጀምርሁ፡፡
ከጌታቸው አሰፋ ቪዲዮ በፊት…….
ኢፌዲሪ ጠ/ሚ እና የኢሕአዴግ ሊ/ር የነበሩት ኃ/ማሪያም ደሳለኝ በድንገት ከመንግስትም ከፓርቲም ኃለፊነታቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ እሳቸውን የሚተካ ሊቀመንበር ለመምረጥ የግንባሩ አባል ድርጅቶች በዝግ ተሰብሰበዋል፡፡ እጪ የመጠቆም ስነ ስርዓቱ ተጀመረ እና ኦቦ ለማ ዶ/ር ዐቢይን በእጩነት አቀረቡ፡፡ በመቀጠልም በቀረቡት እጩ ላይ የድጋፍና የተቃውሞ ድምጾች መሰማት ጀመሩ፡፡ ከሌሎች እጩዎች በተለየ ሁኔታ የዶክተሩ በእጪነት መቅረብ የግንባሩን አባላት ለሁለት ከፍሎ አከራከረ፡፡ረጅም ጊዜም ወሰደ፡፡ ሁሉም በደንብ ቅድመ ዝግጅት ባያደርግም ነገሮች በፍጥነት እየተጓዙ ነበር፡፡ በተለይ የለውጡ ኃይል ሚስጥራዊነቱም፣ ፍጥነቱም በመጨመሩ የማፊያው ቡድን ለክትትል እና ለማሰናከልም ሲቸገር ታየ፡፡በተለይም ገድለን ቀብረናቸዋለን ያሏቸውን ጓድ ዐቢይን የኦህዴድ ሊቀመንበርነቱን ከኦቦ ለማ ተረክበው በድንገት ቤተመንግስቱ በራፍ ላይ ቆመው አገኟቸው፡፡ ደነገጡ፡፡ የጓድ ዐቢይን ከቤተመንግስቱ በፍጥነት የማራቅ ጉዳይም ጓድ ጌታቸው አሰፋ (የወቅቱ የደህንነት ሹም) የቤት ስራ ወሰዱ ፡፡
ከኤርሚያስ ለገሠ ቪዲዮ በፊት…….
የለውጡ ኃይል ስልጣን ጨበጠ፡፡ ኢትዮጵያዊያን ጮቤ ረገጡ፡፡ ኤርሚያስም ኢሳት ቴሌቪዥን በመጠቀም የለውጡን ችቦ አቀጣጠለው፡፡ብዙ ትንታኔዎችን ሰጠ፡፡ ኤርሚያስ ቀድሞ ኢህአዴግን በቃኝ ያለ ብቻ ሳይሆን መጽሐፍትን በመጽሐፍ ጭምር የድርጅቱን ድብቅ ሴራ ያጋለጠ ጀግና ሰው ነው፡፡ የውስጥ ሰው ስለነበር ጥሩ የመረጃ ምንጭ ሆኗል፣ በመጽሐፍቱ የብዙዎችን አይን ገልጧ፡፡ በአጭሩ ይህ ለውጥ እንዲመጣ የበኩሉን ሚና ተጫዎቷል፡፡ ለውጡን ያመጡት ደግሞ የቀድሞ ጓዶቹ በመሆናቸው የ ኤርሚያስ ደስታ ተገቢ ነበር ማለት ተገቢ አስተያየት ነው፡፡በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመረው የአዴፓ ልዑክ አሜሪካ በተገኘበት አንድ አዳራሽ ውስጥ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ክራቫቱን ግጥም አድርጎ ኤርሚያስ ለገሠ ከፊት ለፊት ተሰይሟል፡፡ ጥያቄ ለማቅረብ ዕድል ሲሰጠውም “ አቶ ገዱ ምን እንድናግዛችሁ ትፈልጋላችሁ… አንድ ሁለት ሶስት ብላችሁ ቆጥራችሁ እንድትነግሩኝ እፈልጋለሁ አለ” አቶ ገዱ ሲመልሱም ከእናተ የምንፈልገው ሀገራችሁ ውደዱ፣ ኢንቨስት በማድረግ፣ ዶላር በመላክ ወዘተ ወዘተ አግዙን አሉ፡፡ አቶ ገዱ እንዲደረግላቸው ከሚፈልጉት እገዛ ዝርዝር ውስጥ ኤርሚያስ ለሀገሩ ሊያደርግ የሚፈልገውን “በተለይ ኤርሚያስ ወደ ፖለቲካው ተመልሰህ ከእኛ ጋር ሆነህ ሀገርህን በመምራት ሀገርህንም እኛንም አግዘን” የሚለውን አጣው፡፡ አቶ ገዱ ሳያውቁት ኤርሚያስን አስከፉት፡፡ ከአዳራሹ ውጭም ሌሎችን አማራጮችን ሞከረ ፊት የሚሰጠው አጣ፡፡ በተለይ ከበረከት ጋር ያለውን ቅርበት የሚያውቁት እነ ዶክተር አምባቸው ፊት ነሱት፡፡ አዴፓ ላይ ጥርስ ነከሰ፡፡ በአዴፓ በኩል የቀድሞ ድርጅቱን ኦዲፒን ለመታረቅ የሞከረው ነገር ሲከሽፍ ዶክተር ዐቢይን በሚቀርባቸው ሰው (ስማቸውን መጠቅስ አስፈላጊ ስለሆነ ነው) በኩል ማስታወሻ ላከ፡፡
የጌታቸው አሰፋ የ ቪዲዮ ጌም
ጌቾ ጉባዔው ውስጥ መግባት ባይፈቀድለትም ወደ ጉባኤው ለመግባት ግን የ እሱ መልካም ፈቃድ በቂ ስለነበር ሳይጠበቅ ከጉባኤው አዳራሽ ውስጥ በመገኘት የመጣበትን ጉዳይ አብራራ “ ጓድ ዶ/ር ዐቢይ ሊቀመንበራችን አይሁን…ይሁን እያላችሁ ረጅም ጊዜ በክርክር መወሰዳችሁን ሰማሁና ነው መምጣቴ፡፡ መረጃውን ቀድሜ ባለማደረሴ ዶክተሩ ላይ ጊዜ እንድታጠፉ በማድረጌ ይቅርታ ልጠይቃችሁ አፈልጋለሁ፡፡ የጓድ ዐቢይን ስም ከእጪነትም ከጭንቅላታችሁ አውጡት፡፡ዶክተሩ ላይ ለሀገራችንም ለድርጅታንም ህለውና እጅግ አደጋኛ የሆነ አስደንጋጭ ሚስጥራዊ የቪዲዮ፣ የድምጽና የፎቶግራፍ መረጃዎች የደህንነት መስሪያ ቤቱ ውስጥ ይገኛል ስለዚህ በሰውየው ላይ ጊዜ አታጥፉ አትልፉ አይሆንም ፡፡” አለ፡፡ የጌታቸው ንግግር ለደጋፊዎቻቸው መርዶ ፣ ለተቃወሟቸው ደግሞ የምስራች ሆነ፡፡ ይህም ለሌላ ክርክር በር ከፈተ፡፡ ኦቦ ለማ ቪዲዮውን እዚሁ መጥቶ ካላየነው በአንገቴ ቢላ ይግባ ሲሉ፡፡ አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የሰው ሚስጥር አደባባይ ላይ ማውጣት ተገቢ ስላልሆነ ባይታይ ምርጫቸው እንደሆነ ተናገሩ፡፡ አቶ ደመቀ መኮንን የሚደበቅ ነገር የለም ..ያለህን አምጣውና እዚሁ እንየው አሉ፡፡ ጌታቸው “ ለሀገራችን፣ ለፓርቲያችን በተለይ ለኦህዴድ ክብር ሲባል በእኔ ይሁንባችሁ ቪዲዮ ማየቱ ይቅርባችሁ” ብሎ ጉባዔውን በተደጋጋሚ ተማጸነ፡፡ በተለይ ኦቦ ለማ “ ጓድ ዐቢይ ጥፋት ካለባቸው፣ እንደተባለው የሀገር ክህደት ከፈጸሙ እኔም ሆነ ደርጅቴ ኦህዴድ በጽኑ ልንታገላቸውና ልናወግዛቸው ስለሚገባን ቪዲዮውን ማየት እንፈልጋለን” በማለት የጌታቸውን ተማጽኖ አምረረው ኮነኑት ፡፡ ብዙዎችም ደገፏቸው ስለ ጓድ ዐቢይ ደህንነቱ አለኝ የሚለውን መረጃ ሁሉ ከሳዓት በኋላ አምጥቶ ለጉባኤው እንዲያሳይ በአብልጫ ድምጽ ተወሰነ፡፡ ጌታቸውም በዚህ ጉዳይ ተስማማ፡፡ ዶ/ር ዐቢይ ትንፍሽ ሳይሉ የምሳ ሰዓት ደረሰና ለምሳ ተበተኑ፡፡
የኤርሚያስ ለገሠ የቪዲዮ ጌም ፡- ኤርሜያስ ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐበይ የላከው ማስታወሻ ከሶስት ወር በኋላ ጠ/ሚሩ ጋር ደረሰ፡፡ የማስታወሻዋ ይዘትም በአጭሩ “ ኤርሚያስ ጠ/ሩን በግል ማገዝ እንደሚሻ እና ሀገሩን ማገልግል እንደሚፈልግ በግልጽ አስቀምጧል፡፡ ለጠ/ሚው ሊያድርግ ስለሚችለው ድጋፎች ውስጥም”ከህወኃት ባልተናነሰ የድሮው ብአዴን የአሁኑ አዴፓ ሚስጥራዊ ዶክመንቶች፣ ቪዲዮዎች ወዘተ በእጁ እንደሚገኙና እነዚህን ለጠ/ሚው አሳልፎ መስጠት አንዱ ነው፡፡ ታዲያ ግን ይሄን የሚደርገው ጥሩ ሹመት፣ ቤት እና መኪና እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ሲሟሉለት እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ኤርሚሻ በዚህ አላበቃም ቢሾሙ ጥሩ ነው ያላቸውን የአራት ሰዎችን ስም ዝርዝርም አስፍሯል፡፡
ምሳ ሰዓቱ በዝምታ እና በጭንቀት አሳልፈው ጓድ ጌታቸው አሰፋ ጓድ ዶ/ር ዐቢይ ላይ አለኝ ያለውን ቪዲዮ ለማየት በጉባዔው አዳራሽ ጉብዓተኛው በጊዜ ታድሟል፡፡ ሰዓት መቁጠሩን ቀጥሏል፡፡ ጌታቸው አሰፋም ሆነ ሌላ የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሰው ወደ አዳራሹ ዝር አላሉም፡፡ ጥበቃው ቀጥሏል፡፡ ኦቦ ለማና አቶ ደመቀ መቁነጥነጥ ጀምረዋል፡፡ጌታቸው አሰፋ አመጣዋለሁ ያለውን ቪዲዮ ይዞ ሊመጣ ይቅርና ደብዛው ጠፋ፡፡ በዶ/ር ደብረጺዮን በኩል ሲደወልለትም ስልኩን አጠፋ፡፡ ጉባዔው ወደ ሌላ አጀንዳ ተሻገረ፡፡
መብላቷን ሳታውቅ እጇን ታጠበች እንደሚባለው ኤርሚያስ ለገሠ ወደ ሀገር ውስጥ በሹመት ፣ቤትና መኪና ተሰጥቶት ወደ አዲስ አበባ ሊሄድ እንደሆነ እንደሆነ ለኢሳት ባልደረቦቹ ማስወራት ጀመረ፡፡ የጠ/ሚውን ምልሽ ሳይጠብቅም ሀገር ውስጥ ጃክሮስ አካባቢ በሚኖሩ የቅርብ ሰዎቹ አማካኝነት የቤቱን ጉዳይ በቶሎ እንዲጨርሱለት ወደ ክፍለ ከተማው መልዕክት ላከ፡፡ ያገኘው መልስ ግን የሚፈልገው አይደለም፡፡ ሁሉም ሰው ወደ ሀገሩ የገባው ወዶና ፈቅዶ እንጂ በመደለያ አይደለም …ኤርሚያስም ከፈለገ እንደሌሎቹ መምጣት ይችላል፡፡ የሚል ነበር፡፡ ኤርሚሻ ተበሳጨ፡፡ የክፍለ ከተማ ሰዎችን ልክ ለማስገባትም የጃክሮሶቹን ጉዳይ አስፋጻሚ ወደ አዲስ አበባ ታከለ ም/ል ከንቲባ ታከለ ኡማ ላከ፡፡ ታከለም የመጡት ሁሉ ያረፉት ሆቴል ወይም በየዘመዶቻቸው ቤት ነው፡፡ ፓትሪያሪኩ እንኳ ማረፊያ ቤት የተዘጋጀላቸው ከመጡ በኋላ እንጂ ገና ሳይመጡ አልነበረም፡፡ስለዚህም ለኤርሚያስ ከሁሉም በተለየ ሁኔታ ቤት እና መኪና አዘጋጅተን የምንጠብቅበት ምንም ምክንያት የለም እርማችሁን አውጡ አላቸው፡፡ ኤረሚያስ ታከለ ላይ ቂም ቋጠረ፡፡ ታከለን ልክ አስገባዋለሁ በማለትም ዶክተር ዐቢይ ጋር ማስታወሻ የወሰደለትን ሰው ፈልጎ አገኘው እና የደረሰበትን ጉዳይ ዘርዝሮ ለዶክተር ዐቢይ እንዲያደርስለት ጠየቀው ሰውየው ግን ለኤርሚያስ ባለፈው ለዶክተሩ የላከውን ማስታወሻ ጠ/ሚው ካነበቡ በኋላ “ ይቺ ትሪክ አሁን አለች ” በማለት ቦጫጭቀው ቅርጫት ውስጥ እንዳጣሉት መርዶ አረዳው፡፡ ኤርሚሻ ዶክተር ዐቢይ ላይ ጥርስ ነከሰ፡፡ ተበሳጨ፡፡ ለጠ/ሚው የሹመት እጅ መንሻ “ የህወሓትና የአዴፓ ሚስጥራዊ ቪዲዮ “ አለኝ ብሎ ማስታዋሻ መላኩን ረሳውና “ጠ/ሚው ላይ ሚስጥራዊ ቪዲዮ” አለኝ ወደ ማለት ተሻገረ፡፡በቪዲዮ ከማማለል በቪዲዮ ወደ ማስፈራራት ተሸጋገረ፡፡ ኤርሚያስ አስቂኙ ነገር አለኝ ያለው ቪዲዮ አለ ያለው አበበ ገላው ጋር መሆኑ ነው፡፡ ቀደም ሲል ኤርሚስ እነ አበበ ገላው ላይ “ ሀገሬ ስሄድ እኔ እንደ እናንተ ፔኒሲዮን አላርፍም ” እያለ በጉራው መቀመጫ መቆሚያ አሳጥቷቸው ስለነበር ..አቤ በተራው ኤርሚያስ ላይ ሙድ በመያዝ ሲዝናና የሚውል ሰው ነው፡፡ ኤርሚያስ አሁን ዙሪያውን ሲቃኝ እጁ ላይ ያለው ያላልጨረሰው ( ፕሮሰስ ላይ ያለው) የመኖሪያ ፈቃዱ ( ግሪን ካርዱ) ነው፡፡ የእሷን ፕሮሰስ ለመጨረስ ደግሞ ጠ/ሚውን መጥመድ ይጠቅመኛል ብሎ ድማዳሜ ላይ ደርሷል፡፡ኤርሚያስ ለገሠ ወደ ሀገር ከመውጣታቸው በፊት አለቃየ ስለነበረ በመጠኑ አውቃዋለሁ (አንተ ማለቴ የእድሜ አቻየ በመሆኑ ነው)፡፡ ኤርሚሻ ከፓርቲው በላይ ለአንድ ግለሰብ ያላቸውን ታማኝነት የምናውቅ ካድሬዎች “የሁለት እናቶች ልጅ” የሚል ተቀጥላ ስም አውጥተንለት ነበር፡፡ኤርሚያስ ሁለት እናቶች አምጠው የወለዱት ሰው ነው፡፡ አንዴ ወላጅ እናቱ ሁለተኛ ደግሞ የስምዖን ልጅ በረከት ፡፡አሁን በኢሳት ቴሌቪዥን የምናየውን ኤርሚያስ አምጦ የወለደው ስምዖን ልጅ በረከት ነው፡፡ አምጦ መውለድ ብቻ ሳይሆን የኤርሚያስ ለገሠ.. የፖለቲካ ሰብዕና የተገነባው በስምዖን ልጅ በረከት ነው፡፡ የኤርሚያስ ስሚንቶውም፣ ብሎኬቱም፣ማገሩም፣ ምሰሶውም፣ ጣራውም፣ መንገዱም፣ ሰማዩም ፣ ምድሩም ፣ ዜማውም፣ ቅኝቱም በረከት ነው፡፡በረከት አቡክቶ የሰራት ሰብዕና ደግሞ ሴራ ከኦክስጅን በላይ ትሻለች፡፡ ሴራ ስራዋ ነው፡፡ “ ኤርሚያስ ለገሠ ሆይ ለምትወዳት ሀገርህ ስትል እባክህን ቪዲዮውን ልቀቀው iiiiiii
ጌታቸው አሰፋ ቪዲዮውን ከሰዓት በእርግጠኝነት አመጣለሁ ብሎ ከሄደ በኋላ ምሳ ላይ ጓድ ዐቢይና ጓድ ለማ አብረው ነበር ምሳ የበሉት፡፡ ጓድ ለማ ምግብ መብላት እምቢ ብሎታል፡፡ ጓድ ዐቢይም የጓድ ለማ ጭንቀት ገባውና” አይዞህ አትጨነቅ በህልሜ ስቃዥ ቅዠቴን ጌታቸው አሰፋ ቢቀርጸው እንኳ ከእኔ አንደበት ስለ ሀገሬ መጥፎ ነገር አያገኝም፡፡ሁለት ቪዲዮዎች
///////////////////////////////
////////////////////////////////
/////////////

ጌታቸው አሰፋ ቪዲዮውን ከሰዓት በእርግጠኝነት አመጣለሁ ብሎ ከሄደ በኋላ ምሳ ላይ ጓድ ዐቢይና ጓድ ለማ አብረው ነበር ምሳ የበሉት፡፡ ጓድ ለማ ምግብ መብላት እምቢ ብሎታል፡፡ ጓድ ዐቢይም የጓድ ለማ ጭንቀት ገባውና” አይዞህ አትጨነቅ በህልሜ ስቃዥ ቅዠቴን ጌታቸው አሰፋ ቢቀርጸው እንኳ ከእኔ አንደበት ስለ ሀገሬ መጥፎ ነገር አያገኝም፡፡